1.1የተቋሙ ሥልጣንና ተግባርjjjjjj
የአስፈጻሚ አካላትን ስልጣንና ተግባር እንደገና ለማሻሻል በወጣው አዋጅ ቁጥር 161/2008 መሠረት ቢሮው የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባራት ተሰጥቶታል፣
1.የዞኑን ሁሉንም የሴክተር መዋቅሮች የስራ አፈጻጸም ይገመግማል
2የዞኑን ሁሏቀፍ የልማት ስራዎችን በበላይነት ይከታተላል ያስፈጽማል 3 የዞኑን የፀጥታ ሁኔታ በሚመለከት ጥናትና ክትትል ያደርጋል፤ የፀጥታ መረጃዎችን ይሰበስባል፤ ይተነትናል፤ ያሰራጫል፤ጥቅም ላይ እንዲውሉ ያደርጋል፤ የዞኑን ሰላም ያረጋግጣል፣
2. የዞኑን ሕዝብ ደህንነት፣ ሰላምና ፀጥታ ለማረጋገጥ አግባብነት ካላቸው አካላት ጋር ተባብሮ ይሠራል፣
3. በዞኑ ውስጥ ዘመናዊ የሆነ የፀጥታ መረጃ ፍሰት አያያዝና አደረጃጀት እንዲኖር ስልት ይቀይሳል፤ ይተገብራል፤
4. የፀጥታ መረጃ ለማሰባሰብና ለማስተዳደር የሚረዳ ልዩ የፋይናንስና የበጀት አስተዳደር እንዲሁም የሰው ኃይል አስተዳደር ደንብ በመስተዳድር ምክር ቤት ውሳኔ ተግባራዊ ያደርጋል፤
5. ከአጐራባች ዞኖችና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ፀጥታን በሚመለከት ግንኙነት ያደርጋል፤ በድንበር አካባቢ ያለውን ህብረተሰብ ግንኙነት እንዲሻሻልና እንዲጠናከር የሚረዱ ሥራዎችን ይሠራል፤
6.የወላይታ ዞን በሚያዋስናቸው ጐረቤት ዞኖች የድንበር አካባቢ ሁኔታ በመከታተል መረጃ ያሰባስባል፤ ግጭት እንዳይከሰት የመከላከል ሥራዎችን ከሚመለከተው አካል ጋር በመተባበር ይሠራል፤ ግጭት ሲከሰትም ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመቀናጀት መፍትሔ እንዲያገኙ ያደርጋል፤
7. ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር በግጭት መነሻ ምክንያቶች ላይ ጥናትና ምርምር ያካሂዳል፤ የመፍትሔ ሃሳቦችና የአፈፃፀም ስትራቴጂዎችን ያቀርባል፤ ሲፈቀድም ተግባራዊ ያደርጋል፤
8. በዞኑ በሚገኙ የአስተዳደር እርከኖች መካከል የተሳለጠ አሰራር እና የትብብር መንፈስ መፍጠር እንዲሁም ግጭቶች እንዳይከሰቱ የመከላከል ሥራዎችን ይሠራል፤ ሲከሰቱም በቁጥጥር ሥር ያውላል፤ የግጭቱን መንስዔ አጣርቶ ለሚመለከተው አካል ያቀርባል፤
9. በተለያዩ ሀይማኖትና እምነት ተከታዮች መካከል ሠላምና መከባበር እንዲሰፍን ለማድረግና ግጭትንም ለመከላከል እንዲቻል አግባብ ካላቸው የመንግሥት አካላት፣ የሀይማኖት ተቋማትና ከሌሎች ማናቸውም አካላት ጋር በመተባበር ይሠራል፤
10. በዞኑ ውስጥ በሚንቀሣቀሱ የሀይማኖትና እምነት ተቋማት ተከታዮች መካከል ሠላምና መከባበርን በማጎልበት ግጭትና አለመግባባትን ለመከላከል እንዲቻል አግባብነት ካላቸዉ አካላት ጋር በመተባበር ይሠራል፤ የሀይማኖትና የእምነት ተቋማትን ይመዘግባል፤ ፈቃዳቸዉን ያድሳል፤ ከህግ ውጭ ሆነው ሲገኙ አግባብነት ካላቸዉ አካላት ጋር በመነጋገር ይሰርዛል፤
11. የፀረ-ሰላም ኃይሎችን እንቅስቃሴ ይከታተላል፤ በዚህም የሚፈጠሩ ችግሮችን ለመፍታት የሚያስችሉ አሠራሮችን አጥንቶ ተግባራዊ ያደርጋል፤
12. በየዞኑ ውስጥ ባሉ አስተዳደር እርከኖች መካከል የሚነሱ የማካለል ጥያቄዎች በሠላማዊ መንገድ እንዲፈቱ ያደርጋል፤
13. የየዞኑን የፖሊስና ማረሚያ ፖሊስ ኮሚሽኖችን ሥራዎች በበላይነት ይመራል፤ ይከታተላል፤ ያስተባብራል፤
14. በየዞኑ በተለያዩ የአስተዳደር እርከኖች ከብሔረሰቦች ማንነት ጋር ተያይዘው በሚነሱ የድንበር ማካለል ጉዳዮች በብሔረሰቦች ምክር ቤት የሚሰጡትን ውሣኔዎች ተግባራዊ ያደርጋል፤ አፈፃፀሙን ይከታተላል፤
15. የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ አደጋዎች በአስቸኳይ በቁጥጥር ስር ለማዋል እንዲቻል ሲታዘዝ የፀጥታ ኃይል ያሠማራል፤
16.የተፈጥሮ አደጋ ሲከሰት በሚወሰደው የመከላከል እርምጃ በሴቶችና በህፃናት ላይ ጉዳት እንዳይደርስ የጥንቃቄ እርምጃ ይወስዳል፤
17.የሰው ኃይልን አቅም በመገንባት የህብረተሰቡን ሰላምና ልማት እንዲጠናከር ያደርጋል፤
18. ሚሊሻውን ፀጥታን ለማስከበር በሚያስችል አኳኋን ያደራጃል፤ እንደ አስፈላጊነቱ ከህዝቡና ከሌሎች የፀጥታ ኃይሎች ጋር በቅንጅት የሚሰራበትን ሁኔታ ያመቻቻል፤
19. ሚሊሻው ለረጅም ጊዜ ከምርት ሥራው ሳይነጠል በፀጥታና ሌሎች መንግሥታዊ ሥራዎች ላይ እንዲሰማራ ይከታተላል፤ ይቆጣጠራል፤
20. ዓላማውን ለማስፈፀም የሚረዱ ሌሎች ተግባራትን ያከናውናል፡፡
1.2 በዞኑ የሚሰጡ ዋና ዋና አገልግሎቶች፣
o በፍላጎትና በክፍተት ዳሰሳ ጥናት ለተለዩ ግኝቶች ምላሽ የመስጠት አገልግሎት
o የአሰራርና የሥልጠና ሰነዶችን የማዘጋጀትና ለተጠቃሚ የማዳረስ አገልግሎት፣
o የግንዛቤ ማስጨበጥና ሥልጠናዎችን የመስጠት አገልግሎት፣
o አቤቱታዎችንና ቅሬታዎችን ተቀብሎ ምላሽ የመስጠት አገልግሎት፣
o የሰላም እሴትን የማስረጽና የማጎልበት አገልግሎት፣
o የሰነዶችን ህጋዊነት የማረጋገጥ፣ የምዝገባ፣ ፈቃድ የመስጠት፣ የመሰረዝና የመቆጣጠር አገልግሎት፣
o ብዙኃንና የሙያ ማህበራትና የሀይማኖት ተቋማት ጉባዔዎች እንዲቋቋሙ የመደገፍ፣ የማማከር፣ የማጠናከር፣ የመቆጣጠርና የማብቃት አገልግሎት፣
o በሀይማኖት ሽፋን የሚፈጸም የአክራሪነትና የጽንፈኝነት አመለካከትና ተግባራትን የመከላከል አገልግሎት፣
o የብዙኃን፣ ሙያ ማህበራትንና የሀይማኖት ተቋማት ጉባዔዎችን ተሳትፎና ተጠቃሚነት የማጎልበት አገልግሎት፣
o በግጭት ቅድመ ማስጠንቀቂያና ፈጣን ምላሽ መረጃ መሠረት ፈጣን ምላሽ የመስጠት አገልግሎት፣
o የግጭት ማስተዳደርና መፍታት አገልግሎት፣
o የግጭት መንስዔና ዘላቂ መፍትሄ ጥናት፣ የማስተባበርና የትግበራ አገልግሎት፣
o የሰላም እሴት ግንባታ አደረጃጀቶችን የማደራጀትና የማጠናከር አገልግሎት፣
o በየአስተዳደር እርከኖች የሚነሱ የማካለል ጥያቄ ውሳኔዎችን ተግባራዊ የማድረግ አገልግሎት፣
o በድንበርና አስተዳደር ወሰን አካባቢ የሚከሰቱ ግጭቶችንና የፀጥታ ችግሮችን ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመቀናጀት መፍትሄ የመስጠት አገልግሎት፣
o የፀጥታ ስጋት የሁኔታ ጥናትና ክትትል አገልግሎት፣
o መረጃ የሚሰበሰብባቸውን የስጋት መስኮችና የመረጃ ምንጮችን (ተባባሪዎችን) መለየት፣ ስልቶችን መዘርጋትና ተልዕኮ መስጠት፣
o መረጃ የማሰባሰብ፣ የማደራጀት፣ የመተንተን፣ ሙሉነትን የማረጋገጥ፣ የመተንበይ፣ ጥቅም ላይ የማዋልና ለሚመለከተው አካል የማሰራጨት አገልግሎት፣
o በመረጃ ስብሰባው የተገኙ የፀጥታ ችግሮችና ህገ-ወጥ ድርጊቶችን አፈጻጸም መከታተልና መደገፍ፣
o የፀጥታ መረጃን በዳታ ቤዝ የማስተዳደር አገልግሎት፣
o ምርጥ ተሞክሮዎችን የመቀመርና የማስፋት አገልግሎት
o ክትትል፣ ድጋፍ፣ግብረ መልስና የፋይዳ ዳሰሳ ጥናት የማካሄድ አገልግሎት፣1.1የተቋሙ ሥልጣንና ተግባር
የአስፈጻሚ አካላትን ስልጣንና ተግባር እንደገና ለማሻሻል በወጣው አዋጅ ቁጥር 161/2008 መሠረት ቢሮው የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባራት ተሰጥቶታል፣
1. የክልሉን የፀጥታ ሁኔታ በሚመለከት ጥናትና ክትትል ያደርጋል፤ የፀጥታ መረጃዎችን ይሰበስባል፤ ይተነትናል፤ ያሰራጫል፤ጥቅም ላይ እንዲውሉ ያደርጋል፤ የክልሉን ሰላም ያረጋግጣል፣
2. የክልሉን ሕዝብ ደህንነት፣ ሰላምና ፀጥታ ለማረጋገጥ አግባብነት ካላቸው አካላት ጋር ተባብሮ ይሠራል፣
3. በክልሉ ውስጥ ዘመናዊ የሆነ የፀጥታ መረጃ ፍሰት አያያዝና አደረጃጀት እንዲኖር ስልት ይቀይሳል፤ ይተገብራል፤
4. የፀጥታ መረጃ ለማሰባሰብና ለማስተዳደር የሚረዳ ልዩ የፋይናንስና የበጀት አስተዳደር እንዲሁም የሰው ኃይል አስተዳደር ደንብ በመስተዳድር ምክር ቤት ውሳኔ ተግባራዊ ያደርጋል፤
5. ከአጐራባች ክልሎችና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ፀጥታን በሚመለከት ግንኙነት ያደርጋል፤ በድንበር አካባቢ ያለውን ህብረተሰብ ግንኙነት እንዲሻሻልና እንዲጠናከር የሚረዱ ሥራዎችን ይሠራል፤
6. ክልሉ በሚያዋስናቸው ጐረቤት አገሮች ድንበር አካባቢ ሁኔታ በመከታተል መረጃ ያሰባስባል፤ ግጭት እንዳይከሰት የመከላከል ሥራዎችን ከሚመለከተው አካል ጋር በመተባበር ይሠራል፤ ግጭት ሲከሰትም ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመቀናጀት መፍትሔ እንዲያገኙ ያደርጋል፤
7. ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር በግጭት መነሻ ምክንያቶች ላይ ጥናትና ምርምር ያካሂዳል፤ የመፍትሔ ሃሳቦችና የአፈፃፀም ስትራቴጂዎችን ያቀርባል፤ ሲፈቀድም ተግባራዊ ያደርጋል፤
8. በክልሉ በሚገኙ የአስተዳደር እርከኖች መካከል ግጭቶች እንዳይከሰቱ የመከላከል ሥራዎችን ይሠራል፤ ሲከሰቱም በቁጥጥር ሥር ያውላል፤ የግጭቱን መንስዔ አጣርቶ ለሚመለከተው አካል ያቀርባል፤
9. በተለያዩ ሀይማኖትና እምነት ተከታዮች መካከል ሠላምና መከባበር እንዲሰፍን ለማድረግና ግጭትንም ለመከላከል እንዲቻል አግባብ ካላቸው የመንግሥት አካላት፣ የሀይማኖት ተቋማትና ከሌሎች ማናቸውም አካላት ጋር በመተባበር ይሠራል፤
10. በክልሉ ውስጥ በሚንቀሣቀሱ የሀይማኖትና እምነት ተቋማት ተከታዮች መካከል ሠላምና መከባበርን በማጎልበት ግጭትና አለመግባባትን ለመከላከል እንዲቻል አግባብነት ካላቸዉ አካላት ጋር በመተባበር ይሠራል፤ የሀይማኖትና የእምነት ተቋማትን ይመዘግባል፤ ፈቃዳቸዉን ያድሳል፤ ከህግ ውጭ ሆነው ሲገኙ አግባብነት ካላቸዉ አካላት ጋር በመነጋገር ይሰርዛል፤
11. የፀረ-ሰላም ኃይሎችን እንቅስቃሴ ይከታተላል፤ በዚህም የሚፈጠሩ ችግሮችን ለመፍታት የሚያስችሉ አሠራሮችን አጥንቶ ተግባራዊ ያደርጋል፤
12. በክልሉ ውስጥ ባሉ አስተዳደር እርከኖች መካከል የሚነሱ የማካለል ጥያቄዎች በሠላማዊ መንገድ እንዲፈቱ ያደርጋል፤
13. የክልሉን የፖሊስና ማረሚያ ፖሊስ ኮሚሽኖችን ሥራዎች በበላይነት ይመራል፤ ይከታተላል፤ ያስተባብራል፤
14. በክልሉ በተለያዩ የአስተዳደር እርከኖች ከብሔረሰቦች ማንነት ጋር ተያይዘው በሚነሱ የድንበር ማካለል ጉዳዮች በብሔረሰቦች ምክር ቤት የሚሰጡትን ውሣኔዎች ተግባራዊ ያደርጋል፤ አፈፃፀሙን ይከታተላል፤
15. የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ አደጋዎች በአስቸኳይ በቁጥጥር ስር ለማዋል እንዲቻል ሲታዘዝ የፀጥታ ኃይል ያሠማራል፤
16. የፀጥታ መደፍረስ ወይም የተፈጥሮ አደጋ ሲከሰት በሚወሰደው የመከላከል እርምጃ በሴቶችና በህፃናት ላይ ጉዳት እንዳይደርስ የጥንቃቄ እርምጃ ይወስዳል፤
17. የሚሊሻ ኃይልን አቅም በመገንባት የህብረተሰቡን ሰላምና ፀጥታ እንዲጠበቅ ያደርጋል፤
18. ሚሊሻውን ፀጥታን ለማስከበር በሚያስችል አኳኋን ያደራጃል፤ እንደ አስፈላጊነቱ ከህዝቡና ከሌሎች የፀጥታ ኃይሎች ጋር በቅንጅት የሚሰራበትን ሁኔታ ያመቻቻል፤
19. ሚሊሻው ለረጅም ጊዜ ከምርት ሥራው ሳይነጠል በፀጥታና ሌሎች መንግሥታዊ ሥራዎች ላይ እንዲሰማራ ይከታተላል፤ ይቆጣጠራል፤
20. ዓላማውን ለማስፈፀም የሚረዱ ሌሎች ተግባራትን ያከናውናል፡፡
1.2 በተቋሙ የሚሰጡ ዋና ዋና አገልግሎቶች፣
o በፍላጎትና በክፍተት ዳሰሳ ጥናት ለተለዩ ግኝቶች ምላሽ የመስጠት አገልግሎት
o የአሰራርና የሥልጠና ሰነዶችን የማዘጋጀትና ለተጠቃሚ የማዳረስ አገልግሎት፣
o የግንዛቤ ማስጨበጥና ሥልጠናዎችን የመስጠት አገልግሎት፣
o አቤቱታዎችንና ቅሬታዎችን ተቀብሎ ምላሽ የመስጠት አገልግሎት፣
o የሰላም እሴትን የማስረጽና የማጎልበት አገልግሎት፣
o የሰነዶችን ህጋዊነት የማረጋገጥ፣ የምዝገባ፣ ፈቃድ የመስጠት፣ የመሰረዝና የመቆጣጠር አገልግሎት፣
o ብዙኃንና የሙያ ማህበራትና የሀይማኖት ተቋማት ጉባዔዎች እንዲቋቋሙ የመደገፍ፣ የማማከር፣ የማጠናከር፣ የመቆጣጠርና የማብቃት አገልግሎት፣
o በሀይማኖት ሽፋን የሚፈጸም የአክራሪነትና የጽንፈኝነት አመለካከትና ተግባራትን የመከላከል አገልግሎት፣
o የብዙኃን፣ ሙያ ማህበራትንና የሀይማኖት ተቋማት ጉባዔዎችን ተሳትፎና ተጠቃሚነት የማጎልበት አገልግሎት፣
o በግጭት ቅድመ ማስጠንቀቂያና ፈጣን ምላሽ መረጃ መሠረት ፈጣን ምላሽ የመስጠት አገልግሎት፣
o የግጭት ማስተዳደርና መፍታት አገልግሎት፣
o የግጭት መንስዔና ዘላቂ መፍትሄ ጥናት፣ የማስተባበርና የትግበራ አገልግሎት፣
o የሰላም እሴት ግንባታ አደረጃጀቶችን የማደራጀትና የማጠናከር አገልግሎት፣
o በየአስተዳደር እርከኖች የሚነሱ የማካለል ጥያቄ ውሳኔዎችን ተግባራዊ የማድረግ አገልግሎት፣
o በድንበርና አስተዳደር ወሰን አካባቢ የሚከሰቱ ግጭቶችንና የፀጥታ ችግሮችን ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመቀናጀት መፍትሄ የመስጠት አገልግሎት፣
o የፀጥታ ስጋት የሁኔታ ጥናትና ክትትል አገልግሎት፣
o መረጃ የሚሰበሰብባቸውን የስጋት መስኮችና የመረጃ ምንጮችን (ተባባሪዎችን) መለየት፣ ስልቶችን መዘርጋትና ተልዕኮ መስጠት፣
o መረጃ የማሰባሰብ፣ የማደራጀት፣ የመተንተን፣ ሙሉነትን የማረጋገጥ፣ የመተንበይ፣ ጥቅም ላይ የማዋልና ለሚመለከተው አካል የማሰራጨት አገልግሎት፣
o በመረጃ ስብሰባው የተገኙ የፀጥታ ችግሮችና ህገ-ወጥ ድርጊቶችን አፈጻጸም መከታተልና መደገፍ፣
o የፀጥታ መረጃን በዳታ ቤዝ የማስተዳደር አገልግሎት፣
o ምርጥ ተሞክሮዎችን የመቀመርና የማስፋት አገልግሎት
o ክትትል፣ ድጋፍ፣ግብረ መልስና የፋይዳ ዳሰሳ ጥናት የማካሄድ አገልግሎት፣
.
አግኙን